Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

“የታላቁ የህዳሴ ግድብ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያፋጥን በሕዳሴ ምዕራፍ ውስጥ የሚደምቅ የሀገራችን ብርሃን ነው”:- አቶ ሔኖክ ሙሉነህ

በሐረሪ ክልል በተያዘው 2017 በጀት ዓመት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ የሚውል 15 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትና በክልሉ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ እንደገለጹት፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በመላው ኢትዮጵያውያን ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት እየተገነባ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

ፕሮጀክቱ የብልፅግና ጉዟችንን የሚያፋጥን በሕዳሴ ምዕራፍ ውስጥ የሚደምቅ የሀገራችን ብርሃን ነው ብለዋል።

የክልሉ ህዝብም ባለፉት ዓመታት በዕውቀት፣ በጉልበትና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለግድቡ ስኬታማነት የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

በተያዘው በጀት ዓመትም በክልሉ የሚገኙ መላው ህብረተሰብን በማሳተፍ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 15 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሄኖክ አስታውቀዋል።

በክልሉ ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንዲውል የተያዘው እቅድ ስኬታማ እንዲሆን በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች የውይይት እና የህዝብ ንቅናቄ የመፍጠር ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።

የክልሉ ህዝብ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬታማነት እያከናወኑ የሚገኘውን የድጋፍ ስራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አቶ ሄኖክ ጥሪ አቅርበዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish