Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ ነው-ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሀብ

ሐረር፤መጋቢት 4/2017(ሐክመኮ):-የሴቶች ተሳትፎን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ እንደሚገኝ የሐረሪ ክልል ሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሀብ ገለፁ።

 በሀረሪ ክልል የሴቶች ቀንን በማስመልከት”ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ይረጋገጣል”በሚል መሪ ቃል የአባይ ግድብ የቦንድ ግዢ፤የሴቶች ብድርና ቁጠባና የማህፀን ጫፍ ካንሰር ቅድመ ጥንቃቄና ምርመራ የግንዛቤ ማስጨበጫ መረሀ-ግብር ተካሂዷል።

በመረሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ የሴቶች ቀን በጤና፤ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በሴቶች ህይወት ለውጥ ማምጣት በሚያስችል መልኩ እየተከበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በተለይ የሴቶችን የልማት ህብረት በማጠናከር እና ሞዴል አደረጃጀቶችን በመፍጠር ሴቶች በአካባቢያቸው የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየተሰራ እንደሚገኝ አክለዋል።

ሴቶችን የብድርና ቁጠባ ተጠቃሚ በማድረግ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል በተሰራው ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን በመጠቆም መሰል ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አክለዋል።

በአሁኑ ሰዓትም ሴቶችን በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በማደራጀት፤ምርታማነታቸውን በማሳደግ እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በዕለቱ የህዳሴ ግድብ የቦንድ ሽያጭ እና የቅድመ ካንሰር ምርመራዎች ተካሂዷል።

በክልሉ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን ምክኒያት በማድረግ ለ 30 ቀናት የሚቆይ መርሀ-ግብር ተዘጋጅቶ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰቶት እየተሰራ ይገኛል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish