Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የምትሻገር ሀገር በማይሻገር ሃሳብ እየተናጠች ቆይታለች – ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀስላሴ

የሁለቱ ምክርቤቶች የመክፈቻ ስነስርዓት ላይ ይሬዝዳንቱ ባደረጉት ንግግር የሚታረመውና የሚታረቀው የፖለቲካ ልዩነት እንደማይታረምና እንደማይታረቅ ተደርጎ በመሰራቱ ሀገር በማይጠራ የፖለቲካ ማነቆ እንድትንገላታ ተገዳለች።

የፖለቲካ ወለምታዎችን ለማቅናት ስብራቶችን ለመጠገን ስንጥቃቶችን ለመድፈን ስትጥር ዛሬም ለነገ የታሪክ የቤት ስራ ለማስቀመጥ የሚደረጉት ሙከራዎች የሀገራችንን ፈተና አበርትቶታል ብለዋል።

አሁን ላይ ጋን በጠጠር ይደገፋል የሚለውን ሀገራዊ ብሒል ጠጠር በጋን ይደገፋል ወደሚል ትርጉመ ቢስ አባባል የቀየርነው ይመስላል ሲሉም ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አያይዘውም መንግስታችን በአንድ በኩል ይሄንን ለማረቅ በሌላ በኩል ከዚህ ሃሳብ በእጅጉ የራቀ ትውልድ ለመቅረጽ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህ ነው ክፉን ለማራቅ ምላሳችንን በጥርሳችን እየደገፍን ፈተናዎችን ሁሉ በትዕግስት ማለፍ ተገቢ ብለዋል።

ጥልቅ ማስተዋል፣ ማሰላሰል ፤ አርቆ ማሰብና ትዕግስት የኢትዮጵያ የጽናት ዋልታዎች በመሆናቸው አሰናካይ ሃሳቦችን በማረቅ ወደፊት መራመድ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish