Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የመንግስት የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት እያስገኘ ነው -ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠግን ተግባራዊ ያደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ ።

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ናቸው።

በአዲሱ ዓመት መባቻ የበርካታ ዓመት ቁጭት የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መመረቁ እና በመስከረም ወር መባቻ የከርሰ ምድር ሀብታችን የሆነው የተፈጥሮ ጋዝ መውጣቱ የኢትዮጵያ እድገት መልህቅ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግስት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠግን ተግባራዊ ያደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

ከነጠላ ወደ ብዝሃነት የኢኮኖሚ ልማት በመሸጋገር እየተከናወኑ ባሉ ስራዎች የኢትዮጵያ ኤክስፖርት እያደገ እና ኢኮኖሚው ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ይገኛል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish