Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሐረርን ገጽታ የሚያጎለብቱና የሀዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተከናወኑ ነው – አቶ ኦርዲን በድሪ

የሐረርን ገጽታ የሚያጎለብቱና የሀዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዓለም አቀፍ ቅርስ ጀጎል የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታና ሌሎች ስራዎችን ተመልክተዋል።

እንዲሁም የግንባታ ስራው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት ስራ ጨምሮ የገበያ ማዕከላት፣ የመንገድ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች  እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ውጤታማና የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።

በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የፕሮጀክት ግንባታዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩና የህዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች የመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይ በኮሪደር ልማት የተከናወነው ስራ ከተማዋን የበለጠ የቱሪስት መዳረሻነት አጉልቶ ያሳየ መሆኑንም አመላክተዋል።

በአሁኑ ወቅትም የክልሉን ገጽታ የሚያጎለብቱና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማው ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት በተሻለ ጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም በክልሉ የተገነቡት የገበያ ማዕከላት ህገ-ወጥና የጎዳና ላይ ንግድን በመከላከል አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ በማውጣት ለህብረተሰቡ  በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርብ የሚያስችሉ መሆኑን ገልጸዋል። 

በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish