የሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የማዕረግ እድገት ሰጠ
የሐረሪ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የመቆያ ጊዜያቸውን ለሸፈኑ አባላቱ የማዕረግ እድገት ሰጠ።
የማዕረግ እድገቱን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዩብ አህመድ እና የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ ሰጥተዋል።
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዩብ አህመድ በወቅቱ እንዳሉት፤ የማዕረግ እድገቱ በማረሚያ ቤቱ የተሰጣቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ነው።
በተለይም ታራማዎችን በማነጽና በማረም እንዲሁም ሌሎች የኮሚሽኑን ተግባራትን የመፈፀም ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ አስገንዝበዋል።
የክልሉ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር አድናን አህመድ እንደገለጹት፤ የማዕረግ ዕድገቱን ያገኙት የአገልግሎት ቆይታ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተለይ ማረሚያ ቤቱ ታራሚዎችን በስነ-ምግባርና በሙያ እንዲታነጹ በሚያከናውነው ስራ የአባላቱ አስተዋጽዎ ከፍተኛ እንደነበር አመልክተዋል።
በዚህም የማረሚያ ቤቱ ለ41 አባላቱ ከረዳት ሳጅን እስከ ሙሉ የኮማንደር ማዕረግ እንዲያገኙ መደረጉን ኮሚሽነር አድናን ተናግረዋል።
ማረሚያ ቤቱ እያከናወነ የሚገኘውን የህግ ታራሚዎችን የማረምና የማነጽ ተግባርና ሃላፊነትን ባግባቡ እንደሚወጣም አመልክተዋል።
በእለቱ በኮምሽኑ ታራሚዎችን በማረምና በማነጽ ስራዎች ላይ የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የኮምሽኑ የፖሊስ አባላትና ሲቪል ሰራተኞች አውቅናና የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።
0 Comments