የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል
ከምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል:-
👉ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአለም አርዓያ የሚሆን እጅግ አስደናቂ ተግባር አከናውናለች
👉በለውጡ መንግስት የባህር በር ጥያቄን ወደ መድረክ ማምጣት ተችሏል። መንግስት እያካሄደ የሚገኘው የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ስራም እጅግ የሚበረታታ ነው፥የባህር በር ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ
👉በኢትዮጵያ ከከተማ እስከ ገጠር እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የኢትዮጵያን ገጽታ እጅጉን የሚቀይር ነው፥ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ያለበት ደረጃን በተመለከተ ማብራሪያ ቢሰጥ
👉ሙስና የሰላማችንና የሀገራዊ እድገታችን ጠንቅ ሆኖ እንዳይቀጥል በመንግስት በኩል የተያዘው አቋም ላይ ምን አቅጣጫ ተቀምጧል
👉የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ እድገት እያሳየ የሚገኝ ቢሆንም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማህበረሰብ በኑሮ ውድነት እየተጎ ነው፤
👉ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር በመንግስት በኩል የተሰሩ መልካም ስራዎች እንደተጠበቁ ሆኖ አሁንም የስራ እድል ፈጠራው ተጠናክሮ ቢቀጥል
👉በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ታዳጊዎችን ወደ ትምህርታቸው ለመመለስ የተቀመጠ አቅጣጫ ካለ ማብራሪያ ቢሰጥ
👉በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ማህበረሰቡን ሰላም የሚነሱ ሽፍቶችና ጽንፈኞች ንጹሃንን ሲያግቱ፤ ሲገድሉ ይስተዋላልና መፍትሄ ቢቀመጥ
👉 በሀገሪቱ የዋጋ ንረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሸማቹን የመግዛት አቅም እየተፈታተነ ይገኛል። በተለይ የዚህ ተጎጂው የመንግስት ሰራተኛው ነውና በመንግስት በኩል ምን ታስቧል
👉ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር እና ክልሎችን እርስ በርስ ለማገናኘት ፈጣን የመንገድ መሰረተ ልማቶችን ከመገንባት አንጻር ምን ታስቧል


0 Comments