“የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል በሁሉም የሃገሪቱ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ውስጥ ያለው ባለሙያ ፈጣንና ምላሽ ሰጪ ሊሆን ይገባል” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመታዊ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባኤ ዛሬ ተጀምሯል።
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) መላው የሃገሪቱ የኮሙኒኬሽን መዋቅር ባለፉት ስድስት ወራት የሃገሪቱ ዋና ዋና የልማት እቅዶችና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫዎችን መነሻ በማድረግ በርካታ ውጤቶች እንዲመዘገቡ ማድረጉን አንስተዋል።
ወቅቱ የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት ለዜጎች የእለት ተእለት ኑሮ ጭምር እንቅፋት እስከመሆን የደረሰበት መሆኑንም ሚኒስትሩ አንስተዋል። ይህንን ጫና ለመቋቋም ብቁና ከዘመኑ ጋር አብሮ መጓዝ የሚችል የኮሙኒኬሽን ባለሙያን ማፍራት እንደሚገባ አንስተዋል። ለዚህ ደግሞ የዘርፉን ባለሙያዎች አቅም የሚያጎለብቱ የአቅም ግንባታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በተለይም የኮሙኒኬሽን መዋቅርን ፈጣንና ምላሽ ሰጪ ለማድረግ እንዲሁም የሃገርን ገፅታ መገንባት የሚያስችል አቅም ያለው ማድረግ እንደሚገባ ተገልፇል።
ተቋሙ ባለፉት 6 ወራት ያስቀመጣቸው እቅዶችና ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት በጉባኤው ላይ ቀርበው ከሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ6 ወራት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
ባለፉት 6 ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የስራ አፈፃፀም ላይ የሚመክረውና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከፌደራል ተቋማትና ተጠሪዎቻቸው ጋር የሚካሄደው አመታዊ ጉባኤ ለ2 ቀናት ተነግሯል፡፡
ል ።

0 Comments