የሀዘን መግለጫ
የሀረሪ ክልላዊ መንግሥት በአቶ ዲኒር አህመድ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ በነበሩት አቶ ዲኒር አህመድ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ይገልጻል።
አቶ ዲኒር አህመድ በክልሉ በተለያዩ ተቋማት በኃላፊነት እንዲሁም በክልሉ ከፖሊስ አባልነት እስከ አመራርነት በማገልገል ከህዝብና ከመንግስት የተሰጣቸውን ሚና ሲወጡ ቆይተዋል።
የክልሉ መንግስት ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይመኛል።
0 Comments