የሀረርን ከፍታ እውን ለማድረግ በሚከናወኑ ስራዎች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የከተማው ነዋሪዎች ተናገሩ
የሀረርን ከፍታ እውን ለማድረግ በሚከናወኑ ስራዎች ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።
በከተማው የተከናወኑና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በማስመልከት የሀረር ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት በተለይም በጁገል አለም አቀፍ ቅርስ የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን ለመቀየር የተሰራው ስራ አስደናቂ መሆኑን ተናግረዋል።
ከጁገል አለም አቀፍ ቅርስ ባሻገር በከተማው የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የክልሉን ብልጽግና እውን ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳላቸው ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት።
የልማት ስራዎቹ የከተማዋን መልክ በብዙ ደረጃ መቀየር የቻሉ መሆናቸውን አንስተዋል።
ለዚህም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሰጡት አመራር በታሪክ በአርአያነት የሚነሳ መሆኑን ጠቁመዋል።
ልማቱ የከተማውን ታሪክና ስልጣኔ በሚመጥንና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ለሊትና ቀን እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ ከተማው ለነዋሪውና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ በተለይም ዜጎችን የስራ እድል ተጠቃሚነት ከማጎልበት ባለፈ ለበርካታ አመታት በጅምር ላይ የነበሩ ግንባታዎች እንዲጠናቀቁ ማስቻሉን አክለዋል፡፡
በቀጣይም ሀረርን የበለጠ ለማስዋብ እና ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች ውጤታማነት ድጋፋቸው እንደሚያጠናክሩ አረጋግጠዋል፡፡




0 Comments