Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሀረሪ ክልል የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ታህሳስ 30 2017 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ-የክልሉ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ

ሀረር ታህሳስ 10/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ሲካሄድ የነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ታህሳስ 30 2017 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን የክልሉ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።

በሀረሪ ክልል የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መውጣቱን ተከትሎ ሲካሄድ የነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ መራዘሙን የክልሉ የመንግስት ቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።

በክልሉ በርካታ ውልል ያልፈፀሙ አከራይ ና ተከዮች በመኖራቸው እና በተቀመጠው ግዜ ገደብ ዉሉን ማጠናቀቅ ሳይቻል በመቅረቱ ግዜው መራዘሙ ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

በመሆኑም የግል መኖሪያ ቤት አከራይ እና ተከራዮች የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ በመመዝገብ ከሚደርስባቸው ቅጣት እራሳቸውን እንዲጠብቁ ኤጀንሲው አሳስቧል።

የውል ምዝገባው በየወረዳው የምዝገባ ጣቢያ በመደበኛ የስራ ሰአት የሚካሄድ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች ሳይጨናነቁ በተመቻቸው ሰአት በመሄድ መመዝገብ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish