የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በ2016 በጀት ዓመት የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ዘርፎችን በመጠቀም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገለፀ
የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በ2016 በጀት ዓመት አመርቂ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ማከናወናቸውን አስታውቋል።
የሀረሪ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ በ2016 በጀት ዓመት የኮሙዩኒኬሽን እና ሚዲያን ዘርፎችን በመጠቀም ለህዝቡ መረጃ ተደራሽ ከማድረግና የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ ከማምከን አንፃር አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የክልሉን ህዝብ የሰላም፣ የመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴት እንዲጎለብ በዲጂታል እና በማህበራዊ ሚዲያ የተጠናከረ ስራ መስራት መቻሉን ገልፀው በተለይም የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ስራን በአግባቡ መምራትና ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉን ተናግረዋል።
በማህበራዊ ሚዲያና በአካባቢው ሚገኙ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎች በመጠቀም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።
ዘርፉን በማጠናከርና በማዘመንም የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱን አክለው ገልፀዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ ሴክተሩ በሀገራዊ ገጽታ ግንባታ ሂደት ውስጥ ሰፊ ሚና ያለው መሆኑን ጠቁመው በተለይ በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያጎለብት የኮሙኒኬሽን ስርዓት መዘርጋት መቻሉን ተናግረዋል።
በተለይ ተአማኒነት ያለውና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ለማድረስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ለማከናወን ጥረት ተደርጓል ያሉት አቶ ሄኖክ የሚዲያ ሞኒተሪንግ፣ የህዝብ አስተያየት ጥናት እና የህትመት ዝግጅትና ስርጭት ስራዎች ላይም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።
በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናዎች፣ ዶክመንተሪዎች የአቋም መግለጫዎች በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽነት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ከመፍጠር አንጻር የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ የማስቻል ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል።
በያዝነው የበጀት ዓመትም የነበሩ ጉድለቶችን በማረም በአዲሱ አመት ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ በብቃት ለመወጣት የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

0 Comments