Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ  ከነገ ጀምሮ የመሰረታዊ ድርጅት ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ ያካሂዳል

በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ከነገ ጥር 3 ጀምሮ ዕስከ 8 ለ 6 ተከታታይ ቀናት የመሰረታዊ ድርጅት ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ እንደሚያካሄድ የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገልጸዋል።

ኃላፊው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የመሰረታዊ ድርጅት ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ በክልሉ በከተማና በገጠር በሚገኙ ወረዳዎች ከጥር 3 እስከ ጥር 5 ቀን ድረስ ይሰጣል።

ኮንፈረንሱ በያዝነው ወር ለሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ግብአት የሚሰበሰብበት ነው ብለዋል።

ጉባኤው በተለይም የአባላትን የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት እና አቅምን ለማጠናከር እንዲሁም በክልሉ የተጀመሩ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አስተዳደር ሥራዎች የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ  የሚያስችል መግባባት እና መነሳሳት የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በየደረጃው የሚካሄዱ ኮንፈረንሶች በአባላት በጉጉት የሚጠበቅ እና ከፍ ያለ ተነሳሽነትን የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት ኃላፊው መድረኩ አባላትን ለቀጣይ ተልዕኮዎች የሚያዘጋጅ መሆኑንም ጨምረወሰ ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱ የሀሳብና የተግባር አንድነት የሚጎለብትበት ከመሆኑም ባሻገር ለጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የሚያግዝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በኮንፈረሱ ላይ አባላት በአምስት አጀንዳዎች እንደሚመክሩ የጠቆሙት ኃላፊው አባላት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።

የቅድመ ጉባኤ ውይይቶችና የአባላት ኮንፍረስ እስከ ጉባኤው መዳረሻ ድረስ  ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ነው የገለፁት።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish