የሀረሪ ክልል ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተራና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረበ
የክልሉ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተራና የጥምቀት በዓል በደመቀ እና ባማረ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርባል።
የቢሮ ኃላፊው አቶ ቶፊቅ መሀመድ እንዳሉት በክልሉ በየአመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረው የከተራና የጥምቀት በዓል ባማረና በደመቀ መልኩ በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ለዚህ የፀጥታ ስራ ስኬት በክልሉ የሚገኙ የመከላከያ ፣ የፌደራል ፖሊስ ፣ የሐረሪ ፖሊስ እና የሚሊሽያ አባላት በመቀናጀት በአሉ ባማረና በደመቀ መልኩ በሰላም እንዲጠናቀቅ የተጣለበትን ሀላፊነት በሙሉ ብቃት መወጣታቸውን ገልጸዋል።
ለበዓሉ በሰላም መጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ የሐይማኖት አባቶች ትልቅ አክብሮት አለን ብለዋል።
የከተማው ነዋሪዎች ላደረጉት አስተዋፅኦ ለበዓሉ ድምቀት ለተወጡት ኃላፊነት ምስጋና አቅርበዋል።
ለበዓላቱ ስኬታማነት ሚና ለነበራቸውን የከተማው ህዝብ፣ የፀጥታ እና ህግ አስከባሪ አካላት የሀይማኖት አባቶች ወጣቶችና ለሰላም ቤተሰብ፣ ለኮሚዪኒቲ ፖሊሲንግ ተባባሪዎች አመስግነዋል።
0 Comments