Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የውሀ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ

ሀረር ሀምሌ 10/2016(ሀክመኮ):- የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን እንዳሉት የክልሉን የመጠጥ ውሃ እጥረት ለመቅረፍ የአጭር የረጅም እና መካከለኛ ጊዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል።

በተለይም የፌደራል መንግሥት የክልሉን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ከዚህ ቀደም ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቁመዋል።

እንዲሁም ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እያደረገ የሚገኘው ሳኒቴሽን እና ኢነርጂ ዘርፍ ድጋፍ አድንቀዋል።

የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በበኩላቸው በክልሉ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን የክልሉን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ካለበት ደረጃ ለማሳደግ ብሎም በሳኒቴሽን እና ኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ፣ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሰልጣን ወሊን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish