የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ የማሽላ ኢንሼቲቭ አስጀመሩ
ሀረር ሰኔ 15/2016(ሀክመኮ)የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በክልሉ ሶፊ ወረዳ የማሽላ ኢንሼቲቭ አስጀምረዋል።
የተጀመረው የማሽላ ኢኒሼቲቭ 800 ሄክታር መሬት የሚሸፍን መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር ገልጸዋል።
በዛሬው እለት የተጀመረው የማሽላ ኢንሼቲቭ በ 3 ወራት ጊዜ የሚደርስ መሆኑን ጠቁመዋል
በክልሉ በአጠቃላይ 11 ሺ 650 ሄክታር መሬት በሰብል ለመሸፈን መታቀዱን በመጠቆም ቦለቄ እና ሎዝን ጨምሮ ሌሎች ሰብሎችን ለማምረት በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ገልፀዋል።
በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የክልሉ ምክትል ርእስ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ተገኝተዋል።




0 Comments