የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በጣሊያን ጊዜ የተገነባው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ከደለል እንዲፀዳና አገልግሎት መስጠት እንዲችል ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ
ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ የሀረሪ ክልል ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ለክልሉ ኮንትራክተሮች ማህበር በከተማው በጣልያን ወቅት የተገነባውን የፍሳሽ ማስወገጃ ሲስተም ከደለል እንዲፀዳ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲበቃ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
የፍሳሽ ማስወገጃ በ1930ዎች በጥራት የተገነባ ከፍታው 2 ሚትር ሲሆን ርዝመቱ ደግሞ ከ1.8 ኪሎ ሜትር የሆነ የሀረር የቀደምት ከተሜነት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል።
“ይህ ስራ በቀጣይ በከተማች ለምናለማው ዋነኛው የlandmark ኮሪደር ስፍራ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ነው”።


0 Comments