የሀረሪ ክልላዊ መንግስት እንኳን 1ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ እያለ መልዕክቱን ያስተላልፋል
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን 1ሺህ 446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር እርስ በእርሱ መደጋገፍ እና መቻቻል፣ መተባበርና አብሮነት በማጠናከር ሊሆን ይገባል።
ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላትና የተጠሙትን በማጠጣት እንዲሁም የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን በመተግበር በዓሉን እንዲያከብር የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል።
በተያያዘም ህዝበ ሙስሊሙን ጨምሮ መላው የክልሉ ነዋሪ ሰላምን፣ አብሮነትን፣ መተባበርንና ወንድማማችነት በማጎልበት እንዲሁም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ተግባራት ድጋፉን እንዲያጠናክር የክልሉ መንግስት በዚህ አጋጣሚ ይጠይቃል።
የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ለኢድ አል-አደሃ ዐረፋ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ይመኛል።
መልካም በዓል!
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት
ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ሐረር
0 Comments