የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
የከተራ እና የጥምቀት በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ጥር 10 እና 11 በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነስርዓቶች ይከበራል፡፡
የጥምቀት በዓል አከባበርም በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት/ዩኔስኮ/ በታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም በሰው ልጅ ወካይ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን ይህም ከሀይማኖታዊ በዓልነቱ ባሻገር የሀገሪቱ መልካም ገፅታን ከመገንባትና የቱሪስት ፍሰትን ከማጎልበት አንፃር ጉልህ ሚና ያለው በዓል ነው፡፡
በዓሉ በክልላችን ሲከበርም ሰላምንና አብሮነት በሚያጠናክር እና መከባበርንና መተሳሰብን በሚያጎለብት እንዲሁም ሀገራዊ ገፅታን በሚያሳድግ መልኩ ማክበር ይጠበቃል።
ህዝበ ክርስትያኑ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት፣ የተራቡትን በማብላት የተጠሙ ወገኖችን በማጠጣት እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍ እንደሚያሳልፍ ይተማመናል።
የክልሉ መንግስት በድጋሚ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ የመልካም ምኞት መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
በዓሉም የሰላም፣ የአንድነት፣ የመተሳሰብ፣ የደስታና የፍቅር እንዲሆን ከልብ ይመኛል።
የሀረሪ ክልላዊ መንግስት
ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም
ሐረር
0 Comments