Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ዕዙ ግዳጁን በድል ከመወጣት በተጓዳኝ በልማት ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው -ኢንጅር አይሻ መሀመድ

ሀረር ታህሳስ 5/2017(ሀክመኮ):-የምስራቅ ዕዝ ግዳጁን በድል ከመወጣት በተጓዳኝ በልማት ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ እንደሚገኝ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅር አይሻ መሀመድ ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅር አይሻ መሀመድ መቀመጫውን በሀረር ከተማ ያደረገው የምስራቅ ዕዝ ሰራዊት በኤረር ኢባዳ እያለማው የሚገኘውን የእርሻ ልማት ጨምሮ በሀረር ከተማ የገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በመስክ ምልከታው ላይ እንደገለፁት ዕዙ የሀገርን ዳር ድንበር እያስከበረ ግዳጁን በድል ከመወጣት በተጓዳኝ በልማት ስራዎች ላይም የነቃ ተሳትፎ እያደረገ ነው።

በተለይ በዕዙ እየለማ የሚገኘው እርሻ መንግስት ምርታማነትን በማሳደግ ዕራስን በምግብ ለመቻል እያደረገው ያለውን ጥረት ዕውን ለማድረግ የሚረዳ መሆኑን ገልፀዋል።

ዕዙ ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት በመስጠት በእርሻ ልማት እያከናወነው በሚገኘው ስራ ሰራዊቱ በምግብ ራሱን እንዲችል ከማድረግ ባለፈ የአካባቢውን ማህበረሰብ በምርቱ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ አክለዋል።

በተለይ ዕዙ በግብርና ልማት እያከናወነው በሚገኘው ስራ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን ለአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል።

ዕዙ የሀገርን ዳር ድንበርን ከማስከበር ጎን ለጎን በክልሉ እያከናወናቸው ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ውጤታማነት የክልሉ መንግስት እያደረገው የሚገኝውን ድጋፍም አድንቀዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትሯ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሀረር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘውን ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተመልክተዋል።

ፕሮጀከቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ አገልግሎቱን በማስፋት የክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም ይበልጥ በማጎልበት ከፍተኛ አበርክቶ የሚኖረው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሚኒስትሯ በመጨረሻም የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት በክልሉ የተጀመረውን የቅዳሜ ገበያ የተመለከቱ ሲሆን በገበያው መሰረታዊ የሆኑ ምርቶችን በማቅረብ ማህበረሰቡ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ እያስቻለ ነው ብለዋል።

ገበያው የደላሎችን ጣልቃ ገብነት በማስቀረት አርሶ አደሩን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ እድል የፈጠረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በጉብኝቱ ላይ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የምስራቅ ዕዝ እንዲሁም የሐረር ፌደራል ፖሊስ ሆስፒታል አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish