Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ካስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ወደ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ካስገቡን ጉዳዮች አንዱ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቶች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በማብራሪያቸውም በስራ አጥነት፣ በዋጋ ግሽበት፣ በወጪና ገቢ ንግድ ሚዛን መጓደል ሊገለፅ የሚችል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

ሁለተኛው ለግሉ ዘርፍ የስራ አካባቢው ምቹ አልነበረም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶስተኛው ምርታማነት ነው ብለዋል።

በግብርናም በኢንዱስትሪም ምርታማነታችን ውስን ነበር ሲሉ ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም በርካታ ተግዳሮቶች እንዲስተናገዱ አድርጓል ነው ያሉት።

አራተኛው ተወዳዳሪ የኢኮኖሚ ሁኔታን አልፈጠርንም ያሉ ሲሆን እነዚህን ጉዳዮች ጨክነን በመፍታት የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራቱን መፍታት እንችላለን ብለን ነው ወደ ተግባር የገባነው ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish