ወቅቱን የዋጀ ዘመናዊ ሰራዊት ለመገንባት ርብርብ እየተደረገ ነው-አቶ ኦርዲን በድሪ
ወቅቱን የዋጀ ዘመናዊ የአገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
በሀረሪ ክልል በ2017 አንደኛ ዙር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች የሽኝት መርሃግብር ተካሄደ።
በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የአገር ልማትን እውን በማድረግ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰላም ቁልፍ መሳሪያ ነው።
በመሆኑም የአገር ልማትን ዕውን ለማድረግ የአገራችንን አንድነት እና ሰላም ለማወክ ከውስጥ እና ውጭ የሚደረጉ ሙከራዎችን ማስቆም ብሎም መመከት ይገባል ብለዋል።
የአገራችን አንድነት እና ሰላምን በማረጋገጥ የአገር ልማት እና ብልፅግናን እውን ለማድረግ
በሰው ሀይል እና ቴክኖሎጂ የተደራጀ ጠንካራ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መገንባት ያስፈልጋል።
በተለይ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በአገሪቱ ያሉ ሁኔታዎችን በመጠቀም የአገራችንን ልማት እና ብልፅግና ለማሰናከል ህዝቡን በብሄር እና እምነት ለመከፋፈል እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
በመሆኑም የአገራችንን ሉአላዊንት በማስከበር የምናልመውን ብልፅግና እውን ለማድረግ ጠንካራ ሰራዊት እና ደጀን ህዝብ የያስፈልጋል ብለዋል።
ከለውጡ ወዲህ የአገር መከላከያ ሰራዊቱን የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ሳይሆን ኢትዮጵያን በሚመስል መልኩ ከአዲስ መገንባቱን ገልፀዋል።
በተለይ ወቅቱን የዋጀ ዘመናዊ የአገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
ሰራዊቱ የቴክኖሎጂ እውቀት ባላቸው ብቁ የሰው ሀይል፤ ግብዓት ና አደረጃጀት ለማጠንከር እየተሰራ መሆኑን አክለዋል።
የኢትዮጵያ ህዝቦች በደም ተየሳሰሩ እንደ ስር በአንድ የተገመዱ የማይለያዩ ወንድማማች ህዝቦች መሆናቸውን በመጠቆም ጠላት ይህንን አብሮነት ለማፍረስ እየሰራ ይገኛል።
በመሆኑም ሰራዊቱን ለመቀላቀል ሽኝት የተደረገላቸው አዲስ ምልምሎችም ጠላት ህዝብን በብሄር እና እምነት በመከፋፈል የአገሪቱን ሰላም ለማወክ የሚያደርገወን ጥረት በመመከት ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተለይ ሀረር የምትታወቅበትን የሰላም፤አብሮነት እና የመቻቻል እሴቶች በተመደቡበት አካባቢ ሁሉ ለማህበረሰቡ በማሳየት አርዓያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።





0 Comments