Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ከወጭ ንግድና የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ምንጮች 32 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ከአጠቃላይ የወጭ ንግድና የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ምንጭ 32 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት አካሂዷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስት የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፃምን አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ዲፕሎማሲና በሌሎች ጉዳዮች ጥያቄና አስተያየት አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጪ ንግድን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሳላቸው ጥያቄዎች በበጀት አመቱ 5 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በወጪ ንግድ ለማስገባት ታቅዶ እንደነበር አንስተዋል።

እስካሁን ባለው ሒደት 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ማሳካት መቻሉን ገልጸው የሶስት ቢሊዮን ዶላር ጭማሪ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም በሪሚታንስ ሰባት ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አራት ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ከአገልገሎት 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላት ተገኝቷል ነው ያሉት።

ይህም ባለፈው ዓመት ከሁሉም የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ምንጮች የነበረው ግኝት 24 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው ገልጸዋል።

ዘንድሮ ከአጠቃላይ የወጪ ንግድና የውጭ ምንዛሪ ማግኛ ምንጭ 32 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

ይህ ውጤት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ብልጫ ያለው ስኬት መመዝገቡን የሚያመላክት ሲሆን በዘርፉ የተከናወነው ሪፎርም ውጤት ማምጣቱን በተግባር የሚያረጋግጥ መሆኑንም አብራርተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish