ከአጂፕ ሰላም አደባባይ የሚገነባውን 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ የእረፍት ቀናትን ጨምሮ በምሽት ጭምር በማከናወን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ወደ ስራ ተገብቷል-ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ
ሀረር፣ጥቅምት 19/2018(ሀክመኮ):-በሀረር ከተማ ከአጂፕ ሰላም አደባባይ የሚገነባውን 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ በምሽት ጭምር በማከናወን በፍጥነት ለማጠናቀቅ ወደ ስራ መገባቱን ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።
3.5 ኪ.ሜ ርዝማኔና 30 ሜትር ስፋት ያለውን የጤና ኮሪደሩን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለትራፊክ ፍሰት ክፍት ለማድረግ ወደ ስራ መገባቱን ገልፀዋል።
የመንገድ ግንባታው በተቋራጩ ምክንያት በተያዘለት ግዜ ሳይጠናቀቅ የቆየ መሆኑን በመጠቆም መንግስት በወሰደው የእርምት እርምጃ የግንባታ ስራውን የእረፍት ቀናትን ጨምሮ በምሽት ለማከናወን ወደ ስራ መገባቱን ጠቁመዋል።
የአካባቢው ማህበረሰብና እና የተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት በትእግስት ከመንግስት ጎን ሆነው ላደረጉት እገዛ ልባዊ ምስጋና ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ኮሪደሩ በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት አንደሚደረግ ገልፀዋል።
የህዝባችን እምነትና ትእግስት የበለጠ እንድንተጋ፣ እንዲሁም በከባድ የኃላፊነት ስሜት ቃላችንን እንድንፈጽም አቅም ይሆነናል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልፀዋል።
0 Comments