Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ከአዲስ ፀድቆ ስራ ላይ ለዋለው የአከራይ ተከራይ ደንበ ተፈፃሚነት በትኩረት ይሰራል – አቶ አዩብ አህመድ

ከአዲስ ፀድቆ ስራ ላይ ለዋለው የአከራይ ተከራይ ደንብ ተፈፃሚነት በትኩርት እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ አስታወቁ።

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ ከአዲስ ፀድቆ ስራ ላይ የዋለው የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ደምብን ተግባራዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ደንቡ ፍትሐዊ የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን ለመፍጠር
ያግዛል።

በተለይ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ሁኔታ ባላገናዘበ መልኩ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ክራይ ዋጋ ጭማሪ ስርዓት ለማስያዝ ደንቡ የሚያግዝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በክልሉ ደንቡን ለማስፈፀም የመኖሪያ ቤት ውል እና ምዝገባን በተመለከተ ዝርዝር ጉዳዮችን ያካተተ መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም ጠቁመዋል።

በቀጣይም አከራይ እና ተከራዮች በደንቡ መሰረት ከክልሉ ሰነዶች መረጋገጫ ጋር በመሆን በየወረዳው የአከራይ ተከራይ ውል እንዲፈፀሙ እንደሚደረግ አቶ አዩብ አህመድ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ አዩብ አህመድን ጨምሮ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish