Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች ተፈትተው አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች ተፈትተው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሔደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በአማራ ክልል የማህበረሰቡን የሰላም ሚና በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፥ ማህበረሰቡ ሳይሸሽግ የታጠቁ አካላትን አትግደሉ፣አትግደሉልኝ፣ እናንተም አትሙቱልኝ ማለት አለበት ብለዋል።

ልጆቼን ፈተና እንዳይፈተኑ እንዳይማሩ አትከልክሉ፣እንዳንሰራ አታድርጉ፣ ማዳበሪያ እንዳይመጣ አታድርጉ ማለት አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ይህንን ሰሞኑን የአማራ ህዝብ በቅርቡ አሳይቷል፤ ሰላም ልማት እፈልጋለሁ ብሏል፤ በቃኝ ብሏል ነው ያሉት።

ይህ ለሁሉም ግልፅ መልዕክት ነው። ለዚህ የህዝብ ጥያቄ የከበረ ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል።ማንኛውም ሰው ወደ ስልጣን ሲመጣ ከዚህ ቀደም ምን ሰርተህ ታውቃለህ፣ግብር ከፍለሃል ወይ፣ ማንን አገለገልክ፣ ታማኝ ነህ ወይ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል በማብራሪያቸው።

ህዝቡ ይህን እየጠየቀ ማጥራት አለበት።ማህበረሰቡ የሰላምና የብልሹ አሰራር ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ሚናውን መወጣት እንዳለበት ገልጸው፤ ሰላም ሁልጊዜ የሚገነባ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም የተከሰቱ ግጭቶች ተፈትተው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ አንጻራዊ ሰላም ባይኖር ግብርናው፣ ማዕድኑ፣ ቱሪዝሙ አያድግም ነበር ሲሉ ጠቁመዋል።

አሁንም ቀሪ ችግሮችን በመፍታትና በጋራ በመስራት የሰላምን ዘላቂነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish