ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ ታቀርባለች-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የጋዝ ምርት በቅርቡ ለገበያ እንደምታቀርብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ ባለፉት የመንግስት ስርዓቶች ጋዝ ለማውጣት ሙከራዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል፡፡
መንግስት ከለውጡ በኋላ ጋዝ ለማምረት የሚያስችሉ ፋብሪካዎችን ለመትከል ከግሉ ዘርፍ ጋር ስለመፈራረሙ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አዳዲስ እና እቅም ያላቸው ኩባንያዎች ወደ ዘርፉ እንዲገቡ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
በዚህም በቅርቡ ኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ የጋዝ ምርትን ለገበያ እንደምታቀርብ ገልጸዋል፡፡
ጋዝ የማምረቱ ሂደት የመጀመሪያው ዙር ተጠናቆ በቅርቡ እንደሚመረቅ እና ሁለተኛው የማምረት ሂደትም እንደሚጀመር አስታውቀዋል፡፡
በተመሳሳይ ከ 40 ወራት በኋላ በኢትዮጵያ የማዳበሪያ ፋብሪካ ተመርቆ ስራ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡
የግብርናው ዘርፍ የተሟላና ውጤታማ የሚሆናው የማዳበርያ ፋብሪካ ሲኖር መሆኑን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በማዳበሪያ ምክንያት ምርታማነት ሊወርድ እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡
የማዳበሪያ ፋብሪካውን ለመገንባት በኢትዮጵያ እና በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በርካታ ኢንቨስትመንት ካለው ከናይጄሪያው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ጋር ድርድር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡



0 Comments