አገልግሎቱ ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመረዉን ስራ እያገዘ ነው-ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር
ሐረር፣ሰኔ 7/2017(ሐክመኮ):-የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን አገልግሎት ፣መንግስስት ማህበራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የጀመረዉን ስራ እያገዘ እንደሚገኘ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ገለፁ።
የሐረሪ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ቦርድ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን እየተሰጡ የሚገኙ አገልግሎቶችን ገምግሟል።
በውይይቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር እንደለገፁት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ማህበረሰቡ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት እንዲያገኝ እያስቻለ ነው።
በተለይ ከፍለው መታከም የማይችሉ አቅመ ደካማ ዜጎች አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል አበርክቶው የጎላ መሆኑንም ገልፀዋል።
ይህም መንግስት ማህበራዊ ብልፅግናን በማረጋገጥጥ ጤናማ፣አምራች እና ተወዳዳሪ የሆነ ትውልድን ለማፍራት እያደረገው የሚገኘውን ጥረት እያገዘ እንደሚገኝ አክለዋል።
የማህበረሰብ የጤና መድህን አገልግሎት የጤና ተቋማት አቅምና የሚሰጡትን አገልግሎት እያሳደገ እንደሚገኝመ ጠቁመዋል።
ማህበራዊ ብልፅግናንን ለማረጋገጥ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት አበርክቶው የጎላ በመሆኑ በክልሉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንዲገኝም ጠቁመዋል።
በክልሉ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የተመዘገበውን ስኬት በውጤት አጅቦ ለማስቀጠል ርብርብ እንደሚደረግም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ ጠቁመዋል።

0 Comments