Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል-ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ

ሀረር፣መስከረም 29/2018(ሀክመኮ):-አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የሀረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የደሞዝ ስኬል ማሻሻያ አፈፃፀም መመሪያ ላይ ለተቋም አመራሮች፣የሰው ሀብት ልማት እና ግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተሮች የግንዝቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

የሀረሪ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ዚነት ዩሱፍ በመድረኩ ላይ አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

ተቋማትም ከመስከረም ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ የደሞዝ ማሻሻያውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ መመሪያ አስተላልፈዋል።

ማሻሻያው የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለማቃለል የተደረገ ሲሆን እንደ አገር የተጀመረውን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑንም ገልፀዋል።

የመንግስት ሰራተኛውም ለዜጎች ፍትሀዊ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ሊያሳድግ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የደሞዝ እና የአበል የአከፋፈል መመሪያው በዝርዝር ቀርቦ በአፈፃፀም ሁኔታ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።

Harari #civilservice #newssalary #News #ዜና

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish