Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

አመራሩ በአገልጋይነት መንፈስ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ሊሰራ ይገባል -አቶ ኦርዲን በድሪ

አመራሩ የአገልጋይነት መንፈስን ተላብሶ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ሊሰራ እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ሲያካሂደው የነበረው የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምገማውን አጠናቋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት በክልሉ በሁሉም ዘርፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማስፋት ይሰራል።

በመሆኑም የማህበረሰቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ አመራሩ ለህዝብ ጣያቄ ቅድሚያ በመስጠት በአገልጋይነት መንፈስን ስራዎችን ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የህዝብን ችግር የመቅረፍ ስራ ቅድሚያ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በመጠቆም ለዚህም

አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልም የተቋማት የማስፈፀም አቅምን የማሳደግ ስራ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልፀዋል።

በተለይ በተቋማት ያሉ አደረጃጀቶች እና አሰራሮችን በመፈተሽ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ማነቆ የሆኑ የሌብነት ፤ብልሹ አሰራሮች እና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚታይባቸውን ተጠያቂ ለማድረግ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፤ቀልጣፋ፤ነፃ እና ፍትሀዊ በማድረግ የመልካም አስተዳደርን ዕውን ለማድረግ እንደሚሰራም አክለዋል።

በሌላ በኩል በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡትን አበረታች ውጤቶችን በተሻለ ፍጥነት እና የጥራት ደረጀ እንዲከናወኑ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

ግንባታቸው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችም በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ከገቢ አሰባሰብ ጋር በተገናኘ ከአምናው የተሻለ አፈፃፀም ቢኖርም በሚፈለገው ልክ አለመሰብሰቡን ገልፀዋል።

በቀጣይ መሰብሰብ እያለባቸው ሳይሰበሰቡ የቀሩ የመንግስት ተሰብሳቢዎች በአግባቡ እንዲሰበሰቡ ትኩረት ሰቶ እንዲሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

በሩብ ዓመቱ በግብርና ዘርፍ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰራው ስራ በተለይ በማሽላ ኢንሼቲቭ የተመዘገው ውጤት እንዲሰፋ በትኩረት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

በተለይ በቀጣይ ግዜያት የከተማ ግብርና እና የሌማት ትሩፋት በክልሉ በልዩ ትኩረት የሚሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በስራ ዕድል ፈጠራ፤ኢንቨስትመንት እና ቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ውስንነቶችን በመቅረፍ ውጤታማ ስራ በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በክልሉ ገቢራዊ እየሆነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ በማስፋት የማህበረሰቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እንደሚሰራ እና በተመረጡ የተጎሳቆሉ አካባቢዎች የመልሶ ልማት ስራዎች እንደሚከናወን ጠቁመዋል።

በተለይ በከተማ ፅዳት እና ውበት ውጤት ቢመዘገብም አሁንም ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይ ጊዜያት ዕውቀት እና ክህሎትን የታጠቀ በጥሩ ስነ ምግባር የታነፀ ትውልድን ማፍራት እንደሚገባ በመጠቆም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት ተሰቶ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

ማህበረሰቡን እርስ በዕርስ የሚያቀራርቡ እና የሚያስተሳስሩ የባህል ልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚሰሩም ጠቁመዋል።

ይህን እውን ለማድረግም ማህበረሰቡን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ አዎንታዊ ሰላምን ማስፈን እንደሚገባ ገልፀዋል።

በተለይ የፀጥታ ተቋማት ነፃ እና ገለልተኛ ለህዝብ ወገንተኛ የሆኑ እንዲሆን የሪፎርም ስራ በመስራት በተለይ በፅንፈኞች ላይ አስተማሪ እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነትን ዕውን ለማድረግ እንደሚሰራ አክለዋል።

በክልሉ በክረምት የበጎፈቃድ መርሀ ግብር ማህበረሰቡን የተሻለ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

በተለይ በአረንጓዴ አሻራ 2.5 ሚሊየን ችግኞችን መትከል መቻሉን እና የተሻለ የፅድቀት መጠን መኖሩን በመጠቆም በቀጣይ ስራውን በማስፋት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish