Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

አልሚዎች ግንባታቸውን በህግ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት ይገባል -አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀረሪ ክልል በግንባታው ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎች በህግ በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ መሰረት የግንባታ ስራቸውን አጠናቀው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የግንባታ ሂደትን ሳያጠናቅቁ ኪራይ መስጠት ተጠቃሚዎችን ለአደጋ የሚጋልጥ ከመሆኑም በላይ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችም ያጋልጣል።

በመሆኑም በክልሉ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ አልሚዎቹ ግንባታቸውን እንዲያጠናቅቁ፣ ካልሆነ ደግሞ ተከራዮች የግንባታ ሂደታቸው ወደ ተጠናቀቁ ህንፃዎች እንዲዘዋወሩ ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ ቀጣይነት ያለው እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish