አለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት በትብብር የመስራት ውጤት የታየበት ነው- አቶ ተወለዳ አብዶሽ
ሐረር፣ሰኔ 7/2017(ሐክመኮ):-በርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ኢንሼቲቭ የተከናወነው አለም አቀፉ የጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ስራ በአመራር ቁርጠኝነትና በትብብር የመስራት ውጤት የታየበት መሆኑን የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ።
በርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ኢንሼቲቭ አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ በኮሪደር መልሶ ልማት ስራ ምቹ ማድረግ መቻሉን የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ።
በተለይ የርዕሰ መስተዳድሩ ኢንሼቲቭ መንግስት ቃልን በተግባር ለመተርጎም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየ መሆኑን አክለዋል።
ሐረር የተላያዩ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ማዕከል መሆኗን በመጠቆም የከተማዋን የቀድሞ ስልጣኔ በሚመጥን መልኩ ቅርሱን መልሶ ማልማት መቻሉንም ጠቁመዋል።
በመልሶ ልማት ስራው ቅርሱን ለነዋሪዎች ብሎም ጎብኚዎች ምቹ ከማድረግም በላይ ፅዱና ውብ ገፅታን ማላበስ መቻሉን አክለዋል።
በተለይ በመልሶ ልማቱ በቅርሱ ውስጥ ለዜጎች አማራጭ የመዝናኛ ስፍራዎች መፍጠራቸውንም ጠቁመዋል።
የመልሶ ልማት ስራው አካባቢያዊ ጸጋዎችን በመጠቀም የተከናወነና ለበርካታ ዜጎችም የስራ እድል በመፍጠር የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በጁገል ኮሪደር መልሶ ልማት ተግባር መንግስት ቅርሱን ለዜጎች ብሎም ጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ የሰጠውን ትኩረት የሚያሳይ ነው።
በመልሶ ልማት ስራው ላይ ከገጠር እስከ ከተማ ያለው ማህበረሰብ እና ተቋማት በባለቤትነት ስሜት አሻራቸውን አኑረዋል።
ይህም የአመራር ቁርጠኝነት ኖሮ ማህበረሰብን ባሳተፈ መልኩ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚቻል በተግባር የታየበት ነው ብለዋል።
በቀጣይም አለም አቀፉን የጁገል ቅርስ ጠብቆ ለማቆየት የተጀመረው የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
#UNESCOWorldHeritagesite #HararJugol #corridor
#UNESCOCitiesforPeacePrize #Thelivingmuseum
#World_TourismCitiesFederation
#OrganizationofWorldHeritageCities
#Shuwalidfestival
#Visitharar #VisitEthiopia

0 Comments