ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል- የሐረር ከተማ ነዋሪዎች
ሐረር፣ሰኔ 17/2018(ሐክመኮ):- ብሄራዊ የዲጂታል መታወቂያ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል ሲሉ የሐረር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
በክልሉ በየማዕከላቱ ምዝገባ ሲያካሄዱ ያገኘናቸው ነዋሪዎች እንዳሉት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ እንደሀገርና ግለሰብ የሚያስገኘው ፋይዳ የላቀ ነው።
በምዝገባ ሂደት ፈጣን አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን በተግባር መመልከታቸውን ጠቁመው ህዝቡም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፋይዳን በመገንዘብ ተጠቃሚ መሆን ይገባል ሲሉ ነው የተናገሩት።
የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ በተለይም የሀገርን እና የዜጎችን ደህንነት በማስጠበቅ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።
በክልሉ ሁሉም በሚገኙ ሁሉም የገጠርና ከተማ ወረዳዎች የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል።



0 Comments