Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

ባለፉት የለውጥ አመታት ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን አኳያ የሀይማኖት አባቶች የሰላም አደረጃጀቶች የማህበረሰብ ተወካዮች የማይተካ ሚና እንደነበራቸው ተገለፀ ። 

በክልሉ ያለውን ሰላም በማስቀጠል ዙሪያ ከህብረተሰብ ከተውጣጡ ፣የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶች አባ ገዳዎች የኮሚኒቲ ፖሊሲዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

ባለፉት 7 የለውጥ አመታት ዘላቂ ሰላምን ከማስፈን አኳያ የሀይማኖት አባቶች የሰላም አደረጃጀቶች የማህበረሰብ ተወካዮች የማይተካ ሚና እንደነበራቸው በውይይት በድረኩ በስፋት ተነስቷል። 

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በዉይይት መድረኩ እንደገለፁት ለውጡን ተከትሎ በሀገራችን ከኢኮኖሚ አሻጥር እስከ ጦርነት የደረሰ ተግዳሮቶች አጋጥመዋታል። 

ለዚህም የነጠላ ትርክት ፅፈኝነት ሀገራችንን በተለያዩ ጊዜያት ዋጋ እንዳስከፈላት አውስተው ከለውጡ ወዲህ ከነጠላ ትርክት ወደ አሰባሳቢ ትርክቶች መለወጥ መቻሉን ገልፀዋል ። 

ሀገር እየተጓዘችበት ያለውን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ ፅንፍ የረገጡ አካላት በጋራ በመቀናጀት ሰላሟን ለማደፍረስ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመው ይንን በጋራ መታገል እንደሚገባ አሳስበዋል። 

መንግስት በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ዘርፍች ጠንካ መሆኑን ጠቁመው ቢሆንም ትኩረቱን ከግጭት ወደልማት አዙሮ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። 

በተለይ በልማት በሰላም መንግስት  ለሚሰራቸው ስራ የሀይማኖት ተቋማት ድርሻ ፣ባህላዊ ሸንጎዎች ሚናቸው አይተኬ መሆኑን ጠቁመዋል ። 

በተለይም በመንግስት ተቋም ውስጥ ተቀምጠው ህዝብን ከመንግሥት የሚያቃቅሩ ብልሹ አሰራርን የሚያሰራጩ አካላትን  መንግስት እና ህዝብ በጋራ መታገል እንደሚገባ ጠቁመዋል ። 

የውይይት ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች አስደሳች መሆናቸውን ጠቁመው የልማት ስራዎቹ የህብረተሰብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እና የስራ እድል የሚፈጥሩ መሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል ። 

በሰላም ዙሪያ ክልሉ ለሌችም ተምሳሌት የሚሆን መሆኑን ጠቁመው ለዘላቂነቱ በተለይም የሀይማኖት አባቶች በጋራ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል ። 

በተለይ ህዝብን ከመንግስ የሚያቃቅሩ አካላትን መንግስት መፈተሽ እንደሚገባ እና ብልሹ አሰራርን መታገል እንደሚገባ ጠቁመዋል ። 

መንግስት ህዝቡን ከሀሰተኛ መረጃዎች በመጠበቅ እውነታዎችን መግለጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish