ባለፉት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ፈተና የተመዘገበውን ውጤት ይበልጥ ለማስፋት እየተሰራ ነው-አቶ ዘከሪያ አብዱልአዚዝ
ሀረር፣ጥቅምት 22/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ባለፉት ዓመታት በ12 ኛ ክፍል ፈተና የተመዘገበውን አበረታች ውጤት ይበልጥ ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዘከሪያ አብዱልአዚዝ ገለፁ።
በሀረሪ ክልል የትምህርት ጥራትን በማሻሻል የተማሪ ውጤትን ይበልጥ ለማጎልበት ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ዘከሪያ አብዱልአዚዝ እንደገለፁት በክልሉ የተማሪ የማለፍ ምጣኔ ከግዜ ግዜ እያደገ መጥቷል።
በክልሉ ባለፉት 3 ተከታታይ ዓመታት በ12ኛ ክፍል ፈተና የተመዘገበው አበረታች ውጤትም ለዚ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ብለዋል።
የተመዘገበው ውጤት አበረታች ቢሆንም ለትምህርት ጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት ውጤቱን ይበልጥ ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልዋል።
ለዚህም ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ ትውልድን የሚገነቡና የሚያንጹ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።
በለይ በከተማና ገጠር ትምህርት ቤቶች የትምህርት አመራር ሪፎርም ከማድረግ ጀምሮ ለመምህራን የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅማቸውን ከመገንባት ጀምሮ የትምህርት ሰዓት ብክነትን ለማስቀረት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።
በተለይ ተማሪዎች የትምህርት ሰዓታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ከማድረግ ባሻገር በትርፍ ግዜያቸው የማጠናከሪ ትምህርቶችን እንዲወስዱና ቀደም ሲል የተሰጡ ፈተናዎችን ከመምህራኖቻቸው ጋር በመሆን እንዲለማመዱ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
በገጠርና በከተማ ብሎም በግልና
በመንግስት ትምህርት ቤቶች ያለውን የተማሪዎች ውጤት ልዩነት በጥናት በመለየት ችግሮችን በመቅረፍ የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑንም ገልፀዋል።
ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና በከማና ገጠር ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ለመሰጠት አስፈላጊውን ግብዓት በማሟላት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ተግባራዊ የተደረገው የትምህርት ለትውልድ ፕሮጀክትም ትምህርት ቤቶችን በግብዓት በማደራጀት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት በስፋት እያገዘ መሆኑን ጠቁሟል፡
የትምህርት ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ በመቀየር
ትውልዱን ለመገንባት የተጀመሩ ተግባራት በቀጣይ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ምክትል ቢሮ ሀላፊው አረጋግጠዋል።


0 Comments