በ ከተማው “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ
ሀረር ሰኔ 30/2016(ሀክመኮ):-በሀረር ከተማ “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ ።
የጎዳና ላይ ሩጫውን በንግግር ያስጀመሩት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ሰላም ለሰው ልጆች የመኖር ህልውና መሰረት መሆኑን በመጠቆም መርሀ ግብሩ በተለይ ሀረር የምትታወቅበትን የሰላም፣ የመቻቻልና የአብሮነት እሴቶች የበለጠ የሚጠናከሩበት መሆኑን ገልፀዋል።
ሰላምና የህግ የበላይነት ከሌለ የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰላም ልዩ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይ ህብረተሰቡ ሀረር ለረጅም ዓመታት የምታወቅባቸውን የሰላም፤አብሮነት እና መቻቻል እሴቶቿን መጠበቅና ማስቀጠል እንደሚጠበቅ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጎዳና ላይ ሩጫው ላይ የክልሉ አመራሮች ፣ዳያስፖራዎች እንዲሁም የክልሉ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በእለቱ ውድድሩን በአሸናፊነት ከ 1 እስከ 3 በመውጣት ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ከክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ እጅ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።
በመርሀ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢል ማህዲ፣ የሀረሪ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ፣ የሀረሪ ጉባኤ አፈጉባኤ አቶ ሙህየዲን አህመድን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።





0 Comments