Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በግብርናው ዘርፍ በ30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በግብርናው ዘርፍ ከታረሰው 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛል።

በማብራሪያቸውም፥ በተያዘው በጀት ዓመት የግብርናው ዘርፍ 6 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

በዚህም በግብርናው ዘርፍ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ መነቃቃት መፈጠሩን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማብራሪያቸውም በ2017 በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ነው የገለጹት።

በዚህም በሰብል፣በጥጥ እና በሆልቲካልቸር ተደምሮ ክረምትና በጋ ከታረሰው 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱንም ጠቁመዋል።

የሌማት ትሩፋን በማስመልከት በሰጡት ማብራሪያ፥ ኢትዮጵያ በዓመት 26 ሚሊዮን የዶሮ ጫጩት ታዘጋጅ እንደነበር ጠቁመው፥ በዚህ ዓመት 150 ሚሊዮን ጫጩት ለማዘጋጀት ታቅዷል ነው ያሉት።

የሌማት ትሩፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ተስፋ ሰጪ እድገት የተመዘገበበት ዘርፍ መሆኑን ገልጸው፥ በተያዘው በጀት ዓመት  በሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የሚያስመዘግቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish