Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በዚህ ዓመት 72 ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ሥራ ይጀምራሉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

በዚህ ዓመት 72 ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ስራ እንደሚጀምሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ፤ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

በኢንዱስትሪው ዘርፍ በዚህ ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ይጠበቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ እያንዳንዱ ፋብሪካ ችግሩ እንዲፈታ ከፍተኛ ስራ መከናወኑን ገልጸዋል።

በዚህም የአሌክትሪክ፣ የቴሌኮም፣ የባንክና ሌሎች አገልግሎቶች መቀረፋቸውን ተናግረዋል።

ከመሬት አቅርቦት፣ ከመንግሥታዊ አገልግሎትና ከጉምሩክ ጋር የተያያዙ በርካታ ችግሮች እየተፈቱ ነው ብለዋል።

በዚህ ዓመትም 72 አዳዲስ ከፋብሪካ በላይ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች ሥራ እንደሚጀምሩ ጠቅሰዋል።

ሥራ የሚጀምሩትም 9 የጨርቃጨርቅ፣ 41 የምግብና መጠጥ፣ 4 የኮንስትራክሽንና ኬሚካል፣ 15 የቴክኖሎጂ እና 3 የሚሊተሪ ኢንዱስትሪዎች ናቸው ብለዋል።

ከመከላከያ ጋር ተያይዞ ከውጭ ይመጡ የነበሩ ምርቶችን ከመተካት ባለፈ ለአፍሪካ ገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

እነዚህ 72 ፋብሪካዎች ሥራ ሲጀምሩ ቀድመው ከነበሩት ተጨማሪ ኃብት ያመጣሉ ነው ያሉት።

በሀገራዊ ለውጡ 50 በመቶ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሀገር ውስጥ ባለኃብቶች እንዲያዙ በማድረግ በተኪ ምርትም ከፍተኛ እመርታ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በጥቅሉ በዚህ ዓመት የኢንዱስትሪዎች የምርት አቅም ከ59 በመቶ ወደ 67 በመቶ ዕድገት ይጠበቃል ብለዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish