በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቧል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
በዘንድሮው ዓመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት እያካሔደ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የመንግስትን የ2017 የዕቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው፡፤
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ማዕድንን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሲሰጡም በዘንድሮው አመት ለማዕድን ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለመደገፍ አስችሏል።
በ2016 በጀት ዓመት 4 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ 300 ሚሊዮን ዶላር ገቢ የተገኝ ሲሆን በዘንድሮው አመት ከተገኝው ገቢ ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዘንድሮው አመት 37 ቶን ወርቅ ለውጭ ገበያ በማቅረብ 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኝቱንም አስታውቀዋል።
በዘርፉ ከፍተኛ ለውጥ ለማስመዝገብ የተቻለው በኢትዮጵያ ለብዝሃ ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት መሆኑንም አንስተዋል።
0 Comments