Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በዘንድሮው በጀት ዓመት የአገልግሎት ዘርፉ የ7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ያስመዘግባል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በዘንድሮው በጀት ዓመት የአገልግሎት ዘርፉ የ7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ፤ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው እድገት አለም አቀፍ እውቅና የተቸረው ነው።

በዘንድሮው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ ጠቅላላ አገራዊ ምርት እድገት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ከዚህም ውስጥ ግብርና 6 ነጥብ 1 በመቶ እንደሚያድግ የሚጠበቅ ሲሆን፤ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል ብለዋል።

በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ዘርፉም በተያዘው በጀት ዓመት 12 ነጥብ 8 በመቶ እንዲሁም የአገልግሎት ዘርፉ በ7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘገብ ተናግረዋል።

በተለይም በመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የተደረገው እንቅስቃሴ 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ዓመታዊ እድገት ለማስመዝገብ እንደሚቻል አመላካች አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish