በዓመት እስከ 130 ሚሊየን መንገደኞችን ሊያስተናግድ የሚችል አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ይገነባል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
በዓመት እስከ 130 ሚሊየን መንገደኞችን ሊያስተናግድ የሚችል አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ መገንባት የሚያስችል ጥናት መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብስባውን በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው የኢኮኖሚ ተኮር ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ የቱሪዝምና የአገልግሎት ዘርፍ 7 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ያስመዘግባል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት በማዘዝ ከአፍሪካ ግዙፍ አየር መንገድነቱን ለማስቀጠል በእጥፍ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አሁን ያሉት አውሮፕላን ማረፊያዎች ከ20 እስከ 25 ሚሊየን መንገደኞችን የሚያስተናግዱ ቢሆንም ከ100 እስከ 130 ሚሊየን መንገደኞችን ሊያስተናግድ የሚችል አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ጥናት መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
አሁን ካለው አውሮፕላን ማረፊያ ጋር የባቡር መንገድ በማገናኘት ሁለቱንም በጋራ መጠቀም የሚያስችል አሰራር መታቀዱንም ጠቁመዋል።
ይህም አየር መንገዱ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚጨበጥ ውጤት እያመጣ እንዲቀጥል ያደርገዋል ነው ያሉት።
እንደ እኛ ወደብ አልባ ለሆኑ ሀገራት መሰል ተቋማት የገበያ ብቻ ሳይሆን ስትራቴጂክ ናቸው ሲሉ አብራርተዋል።
0 Comments