በክልሉ 1 ሺ742 የተለያዩ የፊደራል እና የክልል የወንጀል መዝገቦች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ተደርጋል-አቶ አዩብ አህመድ
በሀረሪ ክልል 1 ሺ 742 የተለያዩ የፊደራል እና የክልል የወንጀል መዝገቦች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን መደረጉን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ አዩብ አህመድ ገለፁ።
በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ፍትህን ከማስፈንና የህግ የበላይነትን ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን የሀረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ አዩብ አህመድ ገለፁ።
የፍትሐ ብሔር ክርክርን በተመለከተ በአመቱ በክርክር ሂደት ላይ ከነበሩት 45 መዛግብት ውስጥ በ 15 መዛግብቶች ላይ ውሳኔ በማሰጠት ከ 209 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ማስቀረት ተችሏል ብለዋል።
በዚህም ለፍ/ቤት በቀረቡት የተለያዩ የሙስና እና ኢኮኖሚ ነክ የወንጀል መዝገቦች ላይ ክርክር በማድረግ መንግስት ሊያጣው የነበረዉን 76 ሚሊየን ብር ወደ መንግስት እንዲመለስ መደረጉግ አክለዋል።
የኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች እያደረሱት ካለው ጉዳት አንፃር ኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎችን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል
በቀጣይም ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ጨምሮ በመንግሥት ኢኮኖሚ ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በማጣራት አጥፊዎችን ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የገለፁት።
የህዝብ ሃብትን በክስና በድርድር ለማስመለስ በተሰራ ስራ 298 ሚሊየን ብር ማስመለስ መቻሉንም ገልጸዋል።
በክልሉ 1 ሺ 742 የተለያዩ የፌደራል እና የክልል የወንጀል መዝገቦች ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን መደረጉንም አክለዋል።
በውልና ማስረጃ አገልግሎት አሰጣጥ በክልሉ ህገ-ወጥ የሰነድ ዝግጅትን በመከላከል በአገልግሎቱ ከ 18 ሚሊየን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ ማድረግ ተችሏል።
ከዚህ በተጨማሪም በህገ ውጥ መንገድ በግለሰቦች ተይዞ የነበረን 1.25 ሄክታር የመንግስት መሬት በማስመለስ ወደ መሬት ባንክ ገቢ መደረጉን ገልጸዋል።
በአዲሱ የበጀት ዓመትም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር የህዝብና የመንግስት ጥቅምን በማስጠቅ እንዲሁም በሙስናና ብልሹ አሰራሮችን የመከላከል ስራም በላቀ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
0 Comments