Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ ላይ የታየውን ጉድለት ለመሙላት በትኩረት እየተሰራ ነው አቶ መሀመድ ያህያ

ሀረር ታህሳስ 21/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ገቢን በአግባቡ ለመሰብሰብ ትኩረት ተሰቶ በዘመቻ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ሀላፊ አቶ መሀመድ ያህያ ገለፁ።

በሀረሪ ክልል የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱን ለመምራት የተቋቋመው ኮሚቴ በክልሉ በ5 ወር መሰብሰብ የነበረባቸውና ያልተሰበሰቡ ግብሮችን በአግባቡ መሰብሰብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከረ።

የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያ በበጀት አመቱ ገቢን በመሰብሰብ ረገድ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ቅንጅት  ስራዎች ተጨናክሮ መቀጠል እንዳለበት በውይይቱ  ገልፀዋል።

በተለይ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ግዜ በጥራት እና ፍጥነት ለማጠናቀቅ ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በመሆኑም በገቢ አሰባሰብ ሂደት ያሉ ውስንነቶችን በመቅረፍ መዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ጨምሮ እስከ 500 ሚሊየን ብር በዘመቻው ንቅናቄ በእቅድ የተያዙ ገቢዎችን በአግባቡ ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የሀረሪ ክልል የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ያህያን ጨምሮ የኮሚቴው አባላት ሰፊ ውይይት አድርገው ቀጣይ ስራ ላይ መግባባት ደርሰዋል ።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish