Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 3 መቶ 36 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል-አቶ ሸሪፍ ሙሜ

ሀረር፣ጥቅምት 25/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 3 መቶ 36 ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ሀላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ገለፁ።

መንግስት ለሰራተኞች ያደረገውን የደሞዝ ጭማሪ ተከትሎ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የሀረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ሀላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ እንደገለፁት በክልሉ ምርት በመደበቅ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የክትልል እና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

እየተካሄደ በሚገኘው የቁጥጥር እና ክትትል ስራ ምርት ባሸሸኑና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 3 መቶ 36 ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልፀዋል።

አቅርቦትን በማሳደግ የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ትኩረት ትሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ሸሪፍ ሙሜ በንግድ ተቋማት ላይ የተጀመረው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish