በክልሉ የኮሪደር ልማት ተሞክሮ ሊሆን የሚችል አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል- ኢንጅነር መሀመድአብዱረህማን
ህዳር 21/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ስራ ለሌሎች ተሞክሮ ሊሆን የሚችል አበረታች ውጤቶችማስመዝገብ መቻሉን የኢትዮጽያ መንገዶች ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር መሀመድ አብዱረህማንገለፁ።
በኢትዮጵያ መንገዶች ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር መሀመድ አብዱረህማን የተመራው ልዑካንቡድን በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ተመልክቷል።
ልዑካን ቡድኑ የመስክ ምልከታውን ተከትሎ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ከክልሉ ከፍተኛ የስራአመራሮች ጋር ተወያይቷል።
የኢትዮጽያ መንገዶች ባለ ስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር መሀመድ አብዱረህማን በውይይቱ ላይእንደገለፁት በክልሉ የኮሪደር ልማት ልምድ የሚወሰድበት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በተለይ የኮሪደር ልማቱ በከፍተኛ የአመራር ቁርጠኝነት እና ተነሳሽነት እየተከናወነ የሚገኘ ሲሆን ጥሩ አፈፃፀምየታየበት መሆኑን መመልከት መቻላቸውን ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማቱ የተለያዩ አካባቢዎችን በማገናኘት የመጪውን ግዜ ፍላጎት ከግምት በማስገባት እየተከናወነእንደሚገኝም ገልፀዋል።
በተለይ በክልሉ ፖቴንሽያል የሆኑ አካባቢዎችን በኮሪደር ልማቱ ለማገናኘት እየተሰራ ያለው ስራ አበረታችመሆኑን ጠቁመው ጅምር ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በክልሉ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ከጉዳት ለመጠበቅ እና ዘላቂ ለማድረግ ከሌሎችየመሠረተ-ልማት አውታሮች ጋር በተጣጣመ መልኩ ለማከናወን ቅንጅታዊ አሰራር ትኩረት ሊሰጠውእንደሚገባም ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማቱ ለነዋሪው የተመቸ አካባቢን ለመፍጠር እየተከናወነ እንደሚገኝ በመጠቆም በቀጣይ በክልሉእየተከናወኑ የሚገኙ ልማቶችን በመደገፍ በጥራት እና ፍጥነት ለማከናወን ከክልሉ ጋር በትብብር እንደሚሰሩምገልፀዋል።
እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማቶች መልሶ ማየት የሚገባቸውን ዲዛይኖች ለማስተካከል እንደሚሰራ እናበክልሉ የተመረጡ አካባቢዎችን ለማልማት ወደ ስራ እንደሚገቡም ገልፀዋል።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ በክልሉ እና አካባቢው ያሉየቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተሳሰር ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል።
በተለይ በኮሪደር ልማት ዘርፍ በፌዴራል ደረጃ ለክልሉ የሚደረገው ድጋፍ ከተማዋን የተሻለ ገፅታ በማላበስ ለኑሮእና ስራ ምቹ የሆነች ከተማን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት በፍጥነት ለማከናወን የሚያስችል ሁኔታንእንደሚፈጥር ገልፀዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀረርን ጨምሮ ሌሎች ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችንአጉልቶ ለማሳየት የኮሪደር ልማቱን የሚደግፉ አመራሮችን መመደባቸው ይታወሳል።

0 Comments