Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የኮሪደር ልማት ስራ በላቀ ቁርጠኝነትና ፍጥነት እየተከናወነ ነው፦ አቶ ኦርዲን በድሪ

በሀረሪ ክልል የኮሪደር ልማት ስራዎች በላቀ ቁርጠኝነትና ፍጥነት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ተናገሩ

ርዕሰ መስተዳድሩ በሀረር ከተማ በምሽትም ጭምር እየተሰራ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም ርዕሰ መስተዳድር እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት የተጀመሩ የልማት ስራዎች በተለይም የኮሪደር ልማት ስራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።

የኮሪደር ልማቱ ለዜጎች ፍትሃዊነትና ምቹ የመኖሪያ አካባቢን፤ ለከተሞች ደግሞ  ፅዳትን፣ ውበትንና መሰረተ ልማትን ከማጎናፀፍ ባለፈ የዜጎች የስራ ባህልንና የስራ እድልን እንዲጎለብት እያስቻለ ነው ብለዋል።

በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎች በላቀ ቁርጠኝነት በተሻለ ፍጥነትና ጥራት እየተሰራ ስለመሆኑ አንስተዋል።

የኮሪደር ልማት ስራው አሁን ባለው ግለት ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ነው ያመላከቱት።

ርዕሰ መስተዳድሩ በምልከታቸውም በመርሃግብሩ እየተሳተፉ የሚገኙ ዜጎችን  አበረታተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish