Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል-ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

በሀረሪ ክልል የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉን የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ገለፁ።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በሀረር ከተማ ያለውን የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል። 

ሚኒስትሯ በመስክ ምልከታው እንደገለፁት በክልሉ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ተክቶ ለማምረት በተሰራው ስራ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በተለይ በክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉ የማምረቻ ቦታ እጥረት እና የመሰረተ ልማት ማነቆዎችን ለመቅረፍ የተሰጠው ትኩረት በዘርፉ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል።

በክልሉ ያለው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት የምንፈልጋት ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመፍጠር ከፍተኛ አበርክቶ ያለው መሆኑንም አክለዋል።

በሌላ በኩል ሚኒስትሯ በክልሉ የተገነባውን የአርሶ አደር ምርት መሸጫ መዓከል የጎበኙ ሲሆን መዓከሉ አምራቹን ከሸማቹ ጋር በማገናኘት ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገበያይ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህም ማህበረሰቡ መሰረታዊ ግብዓቶችን በሚፈልገው መጠን እና ጥራት በማቅረብ የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በተለይ አርሶ አደሩ ምርቱን ለመሸጥ ያሳልፈው የነበረውን ውጣውረድ የቀነሰ እና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት በማስቀረት አርሶ አደሩ የልፋቱን ውጤት እንዲያገኝ ያስቻለ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይም በዘርፉ ያሉ ውስንነቶችን በመቅረፍ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን በማስቀጠል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበትና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ሰቶ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመስክ ምልከታው ላይ የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ፣ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish