Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ- ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

ሀረር ሐምሌ 11/2016(ሀክመኮ):- በሀረሪ ክልል የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆናቸውን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ገለፁ።

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የተመራው ልዑክ ከሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በክልሉ እየተገነባ የሚገኘውን የአርሶ አደሮች የግብርና ምርት መሸጫ ማዕከልና ሌሎች ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በመስክ ምልከታው ወቅትም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ እንደገለፁት በክልሉ የአርሶ የአደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሞያዊ ድጋፍ ከመስጠት ጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በክልሉ ምርት እና ምርታማነት በማጎልበት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ብሎም ማህበረሰቡ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ በማስቻል በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ እየተሰሩ የሚገኙ አበረታች ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በከተማው እየተገነባ የሚገኘው የአርሶ አደሮች ምርት መሸጫ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር አምራቹን ከሸማቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት ማህበረሰቡ የፈለገውን ምርት በአንድ ማዕከል እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን አክለዋል።

በተለይ የደላሎችን ጣልቃ ገብነት በማስቀረት አርሶ አደሩ ከምርቱ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም እንዲያገኝ የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሌላ የሀረር ከተማ የሜዲካል ቱሪዝም መሆኗን በማመላከት በከተማው እየተገነባ የሚገኘው የጤና ኮሪደር ልማት የሜዲካል ቱሪዝሙን ይበልጥ እንዲጎለብት የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተማዋን ፅዱ፣ ውብ እና ለኢንቨስትመን ምቹ በማድረግ ረገድ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችም አበረታች መሆናቸውን በመጠቆም የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

በመስክ ምልከታው ላይ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉና የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish