Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የተከናወነው የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት የቱሪስት ፍሰት እንዲጨመር አስችሏል-አቶ ተወለዳ አብዶሽ

ሐረር፤ጥር 23/2017(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል የተከናወነው የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት የቱሪስት ፍሰት እንዲጨመር ማስቻሉን የክልሉ ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገለፁ።

 በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልት የተሰጠው ትኩረት አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት መሆኑን የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በሰጡት መግለጨ ገልፀዋል።

በተለይ ከለወጡ ወዲህ በክልሉ የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት ከጁገል አለም አቀፉ ቅርስ መልሶ ልማት ጀምሮ የጅብ ትርዒት ማሳያ ፓርክ ግንባታዎች በዋናነት መካናወናቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ የተከናወኑ የቱሪዝም መዳረሻዎች ልማት እና እድሳት ኢንሼቲቮች የመዳረሻዎችን ህልውና ከማስጠበቅ ባለፈ የቱሪስት ፍሰቱን እንዲጨምር ያስቻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል የውጪና የሃገር ውስጥ ጎብኚዎች በክልሉ መበራከታቸውን በማሳያነት በማቅረብ።

በተያዘው አመት ብቻ 4 ሺ 991 የውጭ አገር ጎብኚዎች ወደ ክልሉ መምጣታቸውን የገለፁት አቶ ተወለዳ አብዶሽ የቱሪስት ፍሰቱ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 37 በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልፀዋል።

92 ሺ 581 የሀገር ውስጥ ጎብኢዎች በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መጎብኘታቸውንም አክለዋል።

በተለይ እየተከናወነ በሚገኘው የኮሪደር ልማት የተፈጠሩ ምቹ የእግረኛ መንገዶች እና የአረንጓዴ ልማቶች ለቱሪስት ፍሰቱ ምቹ ሁኔታን የፈተጠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ይበልጥ በማጎልበት የቱሪስተ ፍሰት እና ቆይታን ለማሳደግ የቱሪዝም ዘርፉ የሚፈልገውን የመሠረተ ልማቶች እና የሆቴል ቱሪዝም  የማጠናከር ስራ እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል 

በሌላ በኩል በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢኮ ፓርክን በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እኔዲሰጥ ለማስቻል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ሀረር የምትታወቅባቸውን የአብሮነት እሴቶችን ጠብቆ ለማቆየት የተለያዩ ህዝባዊ በዓላትና ሁነቶችን ወንድማማችነትን ይበልጥ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ እንዲከበሩ ድጋፍ ማድረግ መቻሉንም አቶ ተወለዳ አብዶሽ ገልጸዋል ።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish