Skip to content Skip to main navigation Skip to footer

በክልሉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በማስፋት ይሰራል-አቶ ጌቱ ወዬሳ

በሀረሪ ክልል በ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎችን በማስፋት እንደሚሰራ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ በክልሉ በተያዘው የ2017 በጀት ዓመት በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ የክልሉን ገቢ በማስፈት የማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ላይ ርብርብ ይደረጋል።

በተለይ በቱሪዝም ልማት፣የትምህርትእና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነት ላይ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል  ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልፀዋል።

በክልሉ ገቢራዊ እየሆነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራ የከተማውን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር ለክልሉ ህዝብ የኢኮኖሚ ምንጭ መሆን የሚችልበት ሁኔታን ለመፍጠር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ከተማው በፕላን እና ስርዓት እንዲመራ በማድረግ ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ ላይ የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ በቅንጅት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

በክልሉ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ስራም በቀሪው የክረምት ወራት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሰራል ብለዋል።

የሌማት ቱርፋት እና የከተማ ግብርና ስራዎችን በማጠናከር የግብርና ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ስራ በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የሕብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና አንድነት እሴቶች ይበልጥ እንዲጎለብቱ ከማድረግ ጎን ለጎን የክልሉን ሰላም ሁኔታ በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በተለይ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራሮችን በማረም የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በክረምት ወራትም አቅመ ደካሞችን በበጎ ፈቃድ ስራዎች ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አመራሩ ልዩ ትከረት ሰቶ እንዲሰራ አቅጣጫ ያስቀመጡ ሲሆን  የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።

በክልሉ ተግባራዊ እየተደረጉ የሚገኙ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስራዎች ማህበረሰቡን ባሳተፈ መልኩ በብዛት እና ጥራት በግዜ የለኝም መንፈስ በቅንጅት እንዲሰሩ እንደሚሰሩም አቶ ጌቱ ወዬሳ አሳስበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

0 Comments

There are no comments yet

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

en_USEnglish